አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል። አምላክ ሆይ! አንተን ተስፋ እናደርጋለንና ማረን! ማረን! በየቀኑ ጥበቃህ አይለየን፤ በመከራ ጊዜም ታደገን። የአንተ ድምፅ እንደ መብረቅ በሚበርቅበት ጊዜ ሕዝቦች ይሸሻሉ፤ ከግርማህም የተነሣ መንግሥታት ይበተናሉ። አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮ ይሰበሰባል፤ ኩብኩባዎች እንደሚዘሉ ሰዎች በምርኮው ላይ ይረባረባሉ። እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነው! በሰማያትም ይኖራል፤ ለጽዮንም ጽድቅንና ፍትሕን ያጐናጽፋል። የሕዝቡ መሠረት እርሱ ነው፤ ለሕዝቡ ደኅንነትን፥ ጥበብንና ዕውቀትን ይሰጣል፤ እግዚአብሔርን መፍራትም ትልቁ ሀብታቸው ይሆናል።
ትንቢተ ኢሳይያስ 33 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ኢሳይያስ 33:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች