ስለዚህ እርሱ ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ ለመግባት የተቀበልነው ተስፋ ገና የጸና ስለ ሆነ ከእናንተ ማንም ወደዚህ የዕረፍት ቦታ የመግባት ዕድል ሳያገኝ እንዳይቀር ሁላችንም እንጠንቀቅ። መልካሙን ዜና እነርሱ እንደ ሰሙት እኛም ሰምተነዋል፤ ነገር ግን እነርሱ የሰሙትን ቃል በእምነት ስላልተቀበሉት አልጠቀማቸውም። የእርሱ ሥራ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ፦ “እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም ብዬ በቊጣዬ ምዬአለሁ” እንዳለው አሁንም እኛ የምናምነው ወደዚያ እግዚአብሔር ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ እንገባለን፤ ስለ ሰባተኛው ቀን በአንድ ስፍራ “እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ” ተብሎ ተጽፎአል። እንዲሁም በዚሁ ስፍራ ላይ እንደገና “እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም” ይላል። እነዚያ መልካሙን ዜና በመጀመሪያ የሰሙት ባለመታዘዛቸው እግዚአብሔር ወደሚሰጣቸው የዕረፍት ቦታ አልገቡም፤ ሆኖም ወደዚያ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው አንዳንዶች ነበሩ። ይህም አስቀድሞ እንደተባለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ፥ ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ።” ሲል እግዚአብሔር ከብዙ ዘመን በኋላ በዳዊት አማካይነት በተናገረው ቃል “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ቀን በመወሰኑ ተረጋግጦአል። ኢያሱ የዕረፍትን ቦታ ሰጥቶአቸው ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር እንደገና “ዛሬ” በማለት ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር። እንግዲህ ለእግዚአብሔር ሕዝብ የሰንበትን ዕረፍት የመሰለ ዕረፍት ገና ይቀረዋል፤ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ እንዲሁም እግዚአብሔር ወደሚሰጠው ዕረፍት የሚገባ ከሥራው ያርፋል። ስለዚህ ማንም የእነዚያን ሰዎች አለመታዘዝ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደ እግዚአብሔር የዕረፍት ቦታ ለመግባት እንትጋ። የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው፤ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፥ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ የሚቈራርጥ ነው፤ በልብ ውስጥ የተሰወረውንም ሐሳብና ምኞት መርምሮ የሚፈርድ ነው።
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 4 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 4:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos