የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 2:7-21

ኦሪት ዘፍጥረት 2:7-21 አማ05

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ። እግዚአብሔር አምላክ በስተምሥራቅ በኩል በዔደን የአትክልት ቦታን አዘጋጀ፤ የፈጠረውንም ሰው በዚያ እንዲኖር አደረገው። በዚያም ለዐይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ፤ ደግሞም በአትክልቱ ቦታ መካከል ሕይወት የሚሰጥ ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት የሚሰጥ ሌላ ዛፍ ነበረ። የአትክልት ቦታውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔደን ይፈስ ነበር፤ ይህም ወንዝ ከዔደን ከወጣ በኋላ በአራት ወንዞች ይከፈላል። የመጀመሪያው ወንዝ ፊሶን ይባላል፤ እርሱም ወርቅ በሚገኝበት ሐዊላ በሚባለው ምድር ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤ የዚያ አገር ወርቅ ንጹሕ ነበር፤ በተጨማሪም በዚያ አገር ውድ የሆነ ሽቶና የከበሩ ድንጋዮች ይገኛሉ። ሁለተኛው ወንዝ ግዮን ይባላል፤ እርሱም ኢትዮጵያ በምትባል አገር ዙሪያ ይፈስሳል። ሦስተኛው ወንዝ ጤግሮስ ይባላል፤ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈስሳል፤ አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ይባላል። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በዔደን የአትክልት ቦታ አኖረው፤ ይህንንም ያደረገው ሰው የአትክልቱን ቦታ እንዲያለማና እንዲንከባከበው ነው። እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “በአትክልቱ ቦታ ከሚገኙት ዛፎች ሁሉ ፍሬ ልትበላ ትችላለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ በበላህበት ቀን በእርግጥ ስለምትሞት ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት ከሚሰጠው ዛፍ ፍሬ አትብላ።” ቀጥሎም እግዚአብሔር አምላክ “ሰው ብቻውን መኖሩ መልካም አይደለም፤ ስለዚህ ረዳት ጓደኛ እፈጥርለታለሁ” አለ። እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ እንስሶችንና ወፎችን ሁሉ ፈጠረ፤ ምን ዐይነት ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳም ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ያወጣለት ስም መጠሪያው ሆነ። በዚህ ዐይነት አዳም ለወፎቹና ለእንስሶቹ ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ለእርሱ ግን ረዳት ጓደኛ አልተገኘለትም ነበር። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐኑ አጥንቶች አንዱን ወሰደና ባዶውን ቦታ በሥጋ ሞላው፤

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}

Free Reading Plans and Devotionals related to ኦሪት ዘፍጥረት 2:7-21