የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ዕዝራ 3:7-9

መጽሐፈ ዕዝራ 3:7-9 አማ05

እንዲሁም ሕዝቡ ለግንበኞችና ለአናጢዎች የሚከፈለውን ገንዘብ ሰጡ፤ ከሊባኖስ ዛፍ ቈርጠው በኢዮጴ የባሕር ጠረፍ በኩል እንዲልኩላቸው ለጢሮስና ለሲዶና ከተሞች ነዋሪዎች ምግብን፥ መጠጥንና የወይራ ዘይትን ላኩ፤ ይህም ሁሉ የሆነው የፋርስ ንጉሠ ነገሥት ቂሮስ በሰጣቸው ፈቃድ መሠረት ነበር። ስለዚህም በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ወደነበረበት ስፍራ በደረሱበት በሁለተኛው ዓመት፥ በሁለተኛው ወር፥ ዘሩባቤል፥ ኢያሱና ሌሎቹም የሀገራቸው ልጆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ባጠቃላይም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የመጡት ምርኮኞች ሥራውን ጀመሩ። ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ሌዋውያን ሁሉ የቤተ መቅደሱ ሕንጻ ሥራ ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ። ሌዋዊው ኢያሱና ወንዶች ልጆቹ፥ እንዲሁም ዘመዶቹ፥ ቃድሚኤልና ከሖዳዊያ ቤተሰብ ወገን የሆኑ ወንዶች ልጆቹም ሁሉ በአንድነት ተባብረው ቤተ መቅደሱን እንደገና የመሥራቱን ኀላፊነት ተረከቡ፤ የሔናዳድ ዘሮች የሆኑት ሌዋውያንም ይረዱአቸው ነበር።