ከዚህም በኋላ የትሮ እንዲህ አለ፦ “ይህ የምታደርገው ነገር ሁሉ ትክክል አይደለም፤ አንተን ራስህንም ሆነ ሕዝቡን በከንቱ ታደክማለህ፤ ብቻህን ሆነህ ይህን ሁሉ ለመሥራት ይከብድብሃል፤ እነሆ፥ እኔ አንድ ነገር ልምከርህ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ ሕዝቡን ወክለህ በእግዚአብሔር ፊት ጉዳያቸውን አቅርብ፤ አንተ የእግዚአብሔርን ሥርዓትና ሕግ ልታስተምራቸው፥ እንዲሁም እንዴት መኖርና ምን ማድረግ እንደሚገባቸውም ልትገልጥላቸው ይገባል፤ በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው። እነርሱ ሁልጊዜ ተገኝተው ከባድ ያልሆኑ ጉዳዮችን በማየት በዳኝነት ሕዝቡን ያገልግሉ፤ ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ከባድ ጉዳይ ወደ አንተ ያምጡት፤ እነርሱ በዚህ ዐይነት ሸክምህን ቢካፈሉልህ ሥራው ይቀልልሃል። በዚህ ዐይነት ብትሠራና ይህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን ራስህን በከንቱ አታደክምም፤ ሕዝቡም በቀላሉ ጉዳዩ እየተፈጸመለት ወደየቤቱ ይሄዳል።” ሙሴም የዐማቱን ምክር ሁሉ ተቀብሎ በሥራ ላይ አዋለው። ከእስራኤላውያንም ሁሉ መካከል ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ እነርሱንም የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርጎ በሕዝቡ ላይ ሾማቸው።
ኦሪት ዘጸአት 18 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘጸአት 18:17-25
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos