የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:14-17

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:14-17 አማ05

በግልጥ የሚታይ ሁሉ ብርሃን ነው፤ ስለዚህ፦ “አንተ የምታንቀላፋ ንቃ! ከሙታን ተለይተህ ተነሥ! ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሎአል። እንግዲህ እንዴት እንደምትኖሩ በጥንቃቄ አስተውሉ፤ እንደ ጥበበኞች እንጂ እንደ ሞኞች አትኑሩ። ይህ ዘመን ክፉ ስለ ሆነ በማናቸውም አጋጣሚ ጊዜ ተጠቀሙ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።