የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:25-32

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:25-32 አማ05

ስለዚህ ውሸት አትናገሩ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ክፍሎች ስለ ሆንን እርስ በርሳችን እውነት እንናገር። ተቈጡ! በቊጣችሁ ግን ኃጢአት አትሥሩ፤ ቊጣችሁም ሳይወገድ ፀሐይ አይጥለቅባችሁ። ለዲያብሎስም መግቢያ ቀዳዳ አትስጡት። ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ ወዲያ አይስረቅ፤ ይልቅስ ለችግረኞች ይሰጥ ዘንድ ገንዘብ እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካም ነገርን ይሥራ። ከቶ ከአፋችሁ ክፉ ቃል አይውጣ፤ ነገር ግን ለሚሰሙት ደስ የሚያሰኝና ለማነጽ የሚጠቅም ለሰዎችም አስፈላጊ የሆነውን ቃል ተናገሩ። ለምትዋጁበት ቀን ማረጋገጫ እንዲሆናችሁ የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ። መራራነት፥ ንዴት፥ ቊጣ፥ ሁከት፥ ስድብና ማናቸውም ዐይነት ክፋት ሁሉ ከእናንተ ወዲያ ይራቅ። ይልቅስ እርስ በርሳችሁ ደጎችና አዛኞች ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።