ኦሪት ዘዳግም 19:10-12

ኦሪት ዘዳግም 19:10-12 አማ05

ይህንንም የምታደርገው እግዚአብሔር አምላክህ እንድትኖርባት ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ንጹሕ ደም እንዳይፈስስና አንተም የደሙ ተጠያቂ እንዳትሆን ነው። “ነገር ግን አንድ ሰው በጠላትነት ተነሣሥቶ በመሸመቅ ሆን ብሎ በጭካኔ ሌላውን ሰው ከገደለ በኋላ ሕይወቱን ለማትረፍ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፤ ገዳዩ የሚኖርበት ከተማ መሪዎች ሰው በመላክ እነርሱም ነፍሰ ገዳዩን አስመጥተው የሟቹን ደም ለመበቀል መብት ላለው የቅርብ ዘመዱ አሳልፈው ይስጡት።