ኦሪት ዘዳግም 17:16-17

ኦሪት ዘዳግም 17:16-17 አማ05

ያም ንጉሥ ለሠራዊቱ ብዙ ፈረሶች ያሉት መሆን የለበትም፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ስለ አዘዘ ፈረሶችን ለመግዛት ወደ እዚያ ሰዎችን አይላክ። ደግሞም ንጉሡ ብዙ ሚስቶች እንዲኖሩት ማድረግ እግዚአብሔርን ከመከተል ስለሚገታው ንጉሡ ብዙ ሚስቶች እንዲኖሩት አያስፈልገውም፤ ወርቅና ብርም በብዛት አያከማች።