የሐዋርያት ሥራ 7:9-16

የሐዋርያት ሥራ 7:9-16 አማ05

“የያዕቆብ ልጆች በወንድማቸው በዮሴፍ ላይ ቀንተው በግብጽ አገር ባሪያ እንዲሆን ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ፤ ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው። ንጉሡም በግብጽና በቤቱም ሁሉ ላይ አዛዥ አደረገው። በዚያን ጊዜ በግብጽና በከነዓን አገር ሁሉ ላይ ታላቅ ችግር ያስከተለ ራብ ሆነ፤ አባቶቻችንም ምግብ ሊያገኙ አልቻሉም። ያዕቆብም በግብጽ እህል መኖሩን በሰማ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ አባቶቻችንን ወደዚያ ላከ። ዳግመኛ ወደ ግብጽ ተመልሰው በሄዱ ጊዜ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ተገለጠ፤ ቤተ ዘመዱም በፈርዖን ዘንድ ታወቀ። ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብንና ዘመዶቹን ሁሉ ወደ እርሱ አስመጣቸው፤ እነርሱም በጠቅላላው ሰባ አምስት ሰዎች ነበሩ። ስለዚህ ያዕቆብ ወደ ግብጽ ሄደ፤ እርሱና አባቶቻችን እዚያ ሞቱ። ዐጽማቸው ወደ ሴኬም ተወስዶ አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በገንዘቡ በገዛው መቃብር ተቀበረ።