የመቶ አለቃው ግን ከጳውሎስ ምክር ይልቅ የመርከቡ አዛዥና የመርከቡ ባለቤት የሚሉትን ይሰማ ነበር። ያ ወደብ ለክረምት ማሳለፊያ ምቹ ስላልነበረ አብዛኞቹ ሰዎች “ጒዞአቸውን ቀጥለው የሚቻል ቢሆን በሰሜን ምዕራብና በደቡብ ምዕራብ በር ወዳለው ፊንቄ ወደሚባለው የቀርጤስ ወደብ ደርሰን ክረምቱን እዚያ እናሳልፍ” ብለው አሳብ አቀረቡ። አነስተኛ የደቡብ ነፋስ ሲነፍስ ባዩ ጊዜ እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሎአቸው መልሕቃቸውን አንሥተው ጒዞአቸውን ለመቀጠል ተነሡ፤ ከወደቡም ተነሥተው በቀርጤስ አጠገብ አድርገው ጥግ ጥጉን አለፉ።
የሐዋርያት ሥራ 27 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሐዋርያት ሥራ 27:11-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች