የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:8-15

2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:8-15 አማ05

በየአቅጣጫው መከራ ይደርስብናል፤ ግን አንሸነፍም፤ ብዙ ጊዜ ግራ ይገባናል፤ ግን ተስፋ አንቈርጥም፤ ጠላቶች ያሳድዱናል፤ ግን ወዳጆች አጥተን አናውቅም፤ ተመተን እንወድቃለን፤ ግን አንሞትም፤ የኢየሱስ ሕይወት በእኛ ሰውነት እንዲገለጥ በኢየሱስ ላይ የደረሰው ሞት በእኛም ሰውነት ላይ ዘወትር ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት በሟች ሰውነታችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋኑ ስለ ኢየሱስ ሁልጊዜ ለሞት ተላልፈን እንሰጣለን። ስለዚህ እኛ መላልሰን ለሞት ስንጋለጥ እናንተ ግን ለሕይወት ትጋለጣላችሁ። ይሁን እንጂ “አመንኩ፤ ስለዚህ ተናገርኩ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ እኛም ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን። ጌታ ኢየሱስን ከሞት ያስነሣ አምላክ እኛንም ከኢየሱስ ጋር እንደሚያስነሣንና ከእናንተም ጋር በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን። ይህ ሁሉ ለእናንተ ጥቅም የሆነው ጸጋ ተትረፍርፎ ለብዙ ሰዎች በደረሰ መጠን ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆነው ምስጋና እንዲበዛ ነው።

Free Reading Plans and Devotionals related to 2 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:8-15