የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሁለተኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 22

22
የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ
(2ነገ. 8፥25-299፥21-28)
1ዐረቦችና ተከታዮቻቸው ወረራ ባደረጉ ጊዜ በሰፈሩ ላይ አደጋ ጥለው ከሁሉ ታናሽ ከሆነው ከአካዝያስ በቀር የንጉሥ ኢዮራምን ወንዶች ልጆች በሙሉ ገደሉ፤ ስለዚህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ አካዝያስ በአባቱ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ አደረገ፤ 2-3አካዝያስ ዕድሜው ኻያ ሁለት ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ገዛ፤ የንጉሥ አክዓብ ልጅ፥ የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ የልጅ ልጅ የሆነች ዐታልያ ተብላ የምትጠራ እናቱ ወደ ክፋት የሚመራ ምክር ትሰጠው ስለ ነበር አካዝያስ የንጉሥ አክዓብን መጥፎ ምሳሌነት ተከተለ፤ #22፥2 ኻያ ሁለት፦ ወይም አርባ ሁለት። 4ከአባቱ ሞት በኋላ፥ የአክዓብ ቤተሰብ አባላት ለጥፋቱ አማካሪዎቹ ስለ ነበሩ እንደ እነርሱ ክፉ አደረገ፤ 5የእነርሱንም ምክር ተከትሎ በሶርያ ንጉሥ አዛሄል ላይ በተደረገው ጦርነት ከእስራኤል ንጉሥ ኢዮራም ጋር ተባበረ፤ ጦርነቱም በገለዓድ በምትገኘው በራሞት አጠገብ ተደርጎ በዚያ ውጊያ ላይ ኢዮራም ቈሰለ፤ 6ስለዚህ ከቊስሉ ለመፈወስ ተመልሶ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ፤ አካዝያስም ኢዮራምን ለመጠየቅ ወደዚያ ሄደ።
7አካዝያስ ኢዮራምን ሊጠይቅ የሄደው እግዚአብሔር ይህ ጒብኝት የአካዝያስ መጥፊያ እንዲሆን ስለ ፈቀደ ነው፤ አካዝያስ በዚያ በነበረበት ጊዜ እርሱና ኢዮራም የአክዓብን ሥርወ መንግሥት ለማጥፋት እግዚአብሔር የመረጠውን የኒምሺ ልጅ ኢዩን ለመቀበል ወጡ፤ 8ኢዩ በአክዓብ ሥርወ መንግሥት ላይ የእግዚአብሔርን ፍርድ በመፈጸም ላይ በነበረበት ጊዜ አካዝያስን አጅበው ከእርሱ ጋር መጥተው የነበሩትን የይሁዳ መሪዎችና የአካዝያስን ዘመዶች በዚያ አግኝቶ ሁሉንም ገደላቸው። 9አካዝያስንም ፈልገው በሰማርያ ተሸሽጎ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት፤ ነገር ግን የተቻለውን ያኽል እግዚአብሔርን ያገለግል ስለ ነበረው ስለ አያቱ ስለ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ክብር ሲሉ ሬሳውን ቀበሩት።
ከአካዝያስ ቤተሰብ አባላት መካከል መንግሥቱን ሊመራ የሚችል አንድም ሰው አልተረፈም።
የይሁዳ ንግሥት ዐታልያ
(2ነገ. 11፥1-3)
10የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጅዋን መገደል እንደሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባሎች በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ አስተላለፈች። 11አካዝያስ፥ ይሆያዳዕ ተብሎ የሚጠራውን ካህን ያገባች ይሆሼባዕ ተብላ የምትጠራ እኅት ነበረችው፤ እርስዋም ከአካዝያስ ወንዶች ልጆች አንዱ የሆነውን ኢዮአስን ሊገድሉ ጥቂት ቀርቶአቸው ከነበሩት መሳፍንት መካከል በስውር ወስዳ እርሱንና ሞግዚቱን በቤተ መቅደስ አጠገብ በሚገኝ መኝታ ቤት ውስጥ ደበቀቻቸው፤ በዚህም ዐይነት በመደበቅ ኢዮአስን በዐታልያ እጅ ከመገደል አዳነችው፤ 12በዐታልያ ዘመነ መንግሥት ኢዮአስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ስድስት ዓመት ሙሉ ተደብቆ ኖረ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ