1 ወደ ጢሞቴዎስ 3:14-16

1 ወደ ጢሞቴዎስ 3:14-16 አማ05

በቅርብ ጊዜ ለመምጣት ተስፋ ባደርግም እንኳ ምናልባት ከመምጣት የዘገየሁ እንደ ሆነ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንና የእውነት ዐምድ መሠረት በሆነው በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ታውቅ ዘንድ ይህን መመሪያ እጽፍልሃለሁ። የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።