ሳሙኤል ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ ወደ ምጽጳ ጠራ። እንዲህም አላቸው፦ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፦ ‘እናንተን እስራኤልን ከግብጽ አወጣኋችሁ፤ ከግብጽ ኀይልና ከሚጨቊኑአችሁ መንግሥታት ሁሉ ጭቈና አዳንኳችሁ’ ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቀታችሁ ያዳናችሁን አምላካችሁን ትታችኋል፤ እናንተም፦ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አላችሁት። ስለዚህ አሁን በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ”። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱ ነገድ ወደ ፊት እንዲቀርብ አደረገ፤ የብንያምም ነገድ በዕጣ ተመረጠ፤ እንደገናም ሳሙኤል፥ የብንያም ነገድ ቤተሰቦች ሁሉ ወደፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከነዚያም የማጥሪ ቤተሰብ በዕጣ ተመረጠ፤ በመጨረሻም የማጥሪ ቤተሰብ ወንዶች ወደፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከእነርሱም መካከል ለቂስ ልጅ ለሳኦል ዕጣ ወጣ፤ እነርሱም በፈለጉት ጊዜ ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህም እነርሱ “ሌላ የቀረ ይኖር ይሆን?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም “ሳኦል እነሆ በዕቃ መካከል ተደብቆ ይገኛል” ሲል መለሰላቸው። ስለዚህም እነርሱ ፈጠን ብለው በመሄድ ከተሸሸገበት አውጥተው ወደ ሕዝቡ አመጡት፤ ሕዝቡም ሳኦል በትከሻውና በቁመት ከሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ተመለከቱ፤ ሳሙኤልም ሕዝቡን “እግዚአብሔር የመረጠው ሰው እነሆ ይህ ነው! ከእኛም መካከል እርሱን የሚስተካከለው የለም” አለ። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ ይሁን!” አሉ። ሳሙኤልም ለሕዝቡ፥ ለአንድ ንጉሥ ሊደረግለት የሚገባውን ሥርዓት አስረዳቸው፤ ያንንም በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጠው፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡን ሁሉ ወደየቤቱ አሰናበተ፤ ሳኦልም በጊብዓ ወደሚገኘው ቤቱ ተመልሶ ሄደ፤ እግዚአብሔር ልባቸውን ያነሣሣው ኀያላንም ሳኦልን ተከትለው ሄዱ፤ ነገር ግን አንዳንድ ሥርዓተ አልባዎች “አሁን ይህ ሰው እኛን ለማዳን ይችላል?” ተባባሉ፤ እርሱንም በመናቅ ምንም ዐይነት ገጸ በረከት ሳያመጡለት ቀሩ። ሳኦል ግን ዝም አለ።
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 10 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 10:17-27
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos