ክርስቶስ በሥጋው መከራ የተቀበለ ስለ ሆነ እናንተም የጦር መሣሪያን እንደ ታጠቀ ሰው በዚህ ሐሳብ በርትታችሁ ተዘጋጁ፤ በሥጋው መከራን የተቀበለ ሰው ኃጢአት መሥራትን አቋርጧል። ከእንግዲህ ወዲህም በቀሪው ምድራዊ ኑሮው የሚኖረው የሥጋን ክፉ ምኞት በማድረግ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም ነው። አሕዛብ እንደሚያደርጉት በስድነት፥ በፍትወት፥ በስካር፥ ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያ፥ ያለ ልክ ጠጥቶ በመጨፈርና አጸያፊ በሆነ የጣዖት አምልኮ ያሳለፋችሁት ዘመን ይበቃል። አሁን ግን በዚህ ነገር አለመጠን ከእነርሱ ጋር በመቅበጥ ባለመሳተፋችሁ ይደነቃሉ፤ ይሰድቡአችኋልም። ነገር ግን በሕይወት ባሉትና በሞቱት ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው ለእርሱ መልስ ይሰጡበታል። ለሙታን ሳይቀር ወንጌል የተሰበከውም በዚህ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት በሥጋቸው እንደ ሰው ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ በመንፈሳቸው ግን እግዚአብሔር በሚኖረው ዐይነት በሕይወት ይኖራሉ። እንግዲህ የሁሉ ነገር መጨረሻ ቀርቦአል፤ በትጋት መጸለይ እንድትችሉ የረጋ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በመጠንም ኑሩ። ፍቅር ብዙ ኃጢአትን ስለሚሸፍን ከሁሉ በላይ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
1 የጴጥሮስ መልእክት 4 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 የጴጥሮስ መልእክት 4:1-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos