የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 የዮሐንስ መልእክት መግቢያ

መግቢያ
መጀመሪያው የሐዋርያው የዮሐንስ መልእክት ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች አሉት። እነርሱም አንባቢዎቹ ከእግዚአብሔርና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድነት እንዲኖራቸው ለማበረታታትና ይህንንም አንድነት ሊያጠፋ ከሚችል ሐሰተኛ ትምህርት እንዲርቁ ለማስጠንቀቅ ነው። በዚያን ጊዜ የተከሠተው ሐሰተኛ ትምህርት ክፋት የሚመነጨው ከግዙፉ ዓለም ጋር በሚደረገው ግንኙነት ስለ ሆነ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ከቶ ሰው ሊሆን ወይም የሰብአዊነት ባሕርይ ሊኖረው አይችልም የሚል ነበር። እነዚያ መምህራን “መዳን ማለት ለዓለማዊ ኑሮ ከመጨነቅ ነጻ መውጣት ነው” ይሉ ነበር፤ ከዚህም ጋር “የግብረ ገብነት አቋምም ሆነ ለሌላው ሰው ፍቅር ማሳየት ከመዳን ጋር ምንም ግንኙነት” የለውም ይሉ ነበር።
ጸሐፊው ይህን ትምህርት በመቃወም ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ነው፤ በኢየሱስ የሚያምኑና እግዚአብሔርን የሚወድዱ ሁሉ እርስ በርሳቸውም መዋደድ ይኖርባቸዋል በማለት አስረድቶአል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-4
ብርሃንና ጨለማ 1፥5—2፥29
የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች 3፥1-24
እውነትና ስሕተት 4፥1-6
የፍቅር ግዴታ 4፥7-21
ድል አድራጊው እምነት 5፥1-21

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ