1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የጻፈላቸው የመጀመሪያው መልእክት የተጻፈው በቆሮንቶስ ባቋቋመው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ ክርስትና ሕይወትና እምነት ተነሥቶ ለነበረው ችግር መፍትሔ ለማስገኘት በማሰብ ነው። በዚያን ጊዜ ቆሮንቶስ ዓለም ዐቀፋዊት የሆነች የግሪክ ከተማ ከመሆንዋም በላይ አካይያ ለተባለ የሮም ግዛት ዋና ከተማ ነበረች። ይህች ከተማ ታላቅ በሆነ የንግድ እንቅስቃሴ፥ በደረጀ ባህል፥ እጅግ በመስፋፋት ላይ በነበረ ምግባረ ብልሹነትና በሃይማኖቶች ብዛት የታወቀች ነበረች።
ሐዋርያው በተለይ ያተኰረው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ስለ ነበረው መከፋፈል፥ ስለ ምግባረ ብልሹነት ሕይወት፥ ስለ ዝሙትና ስለ ጋብቻ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችና ስለ ትንሣኤ ነበር፤ እንዲሁም ሐዋርያው የምሥራቹን ቃል በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ በማተኰር በጥንቃቄ ያቀርባል።
“ፍቅር” እግዚአብሔር ለሕዝቡ ከሰጣቸው ስጦታዎች የበለጠ መሆኑን የሚገልጠው ዐሥራ ሦስተኛው ምዕራፍ ከዚህ መጽሐፍ እጅግ ታዋቂ የሆነው ክፍል እንደ ሆነ ይገመታል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-9
በክርስቲያኖች መካከል የተነሣ መከፋፈል 1፥10—4፥21
ምግባረ ብልሹነትና የቤተሰብ ሕይወት 5፥1—7፥40
ክርስቲያኖችና የክርስቲያን እምነት ያልተቀበሉ። 8፥1—11፥1
የቤተ ክርስቲያን ሕይወትና የአምልኮ ሥርዓት 11፥2—14፥40
የክርስቶስና የአማኞች ትንሣኤ 15፥1-58
በይሁዳ ላሉ ለተቸገሩ ክርስቲያኖች ርዳታ 16፥1-4
ማጠቃለያ 16፥5-24
Currently Selected:
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997