እኔ ነጻነት ያለኝ ሰው አይደለሁምን? እኔ ሐዋርያ አይደለሁምን? እኔ ጌታችንን ኢየሱስን አላየሁትምን? እናንተስ በጌታ የሥራዬ ውጤት አይደላችሁምን? በጌታ የሐዋርያነቴ ማረጋገጫ ማኅተም እናንተ ስለ ሆናችሁ ለሌሎቹ እንኳ ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተ ግን በእርግጥ ሐዋርያ ነኝ። “የሐዋርያነት መብት የለህም” ብለው የሚተቹኝ ቢኖሩ የምሰጠው መልስ ይህ ነው፤ እኛ ምግብና መጠጥ የማግኘት መብት የለንምን? እንደ ሌሎች ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ጴጥሮስም ክርስቲያን ሚስት አስከትለን የመዘዋወር መብት የለንምን? ወይስ በሥራ እየጣርን መኖር የሚገባን በርናባስና እኔ ብቻ ነንን? ያለ ደመወዝ በራሱ ገንዘብ በወታደርነት የሚያገለግል ማነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላስ ማነው? መንጋ እየጠበቀ የመንጋውን ወተት የማይጠጣ ማን ነው? ይህን የምናገረው በሰው አስተሳሰብ ብቻ ነውን? ሕግስ እንዲህ ይል የለምን? “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር” ተብሎ በሕግ ተጽፎአል፤ ታዲያ እግዚአብሔር ይህን ያለው ስለ በሬዎች በማሰብ ነውን? እግዚአብሔር ይህን ያለው ስለ እኛ በማሰብ አይደለምን? የሚያርስ ገበሬ በተስፋ እንዲያርስ፥ የሚያበራይም በተስፋ እንዲያበራይ፥ በዚህ ዐይነት ሁሉም ድርሻውን እንዲያገኝ ይህ የተጻፈው በእርግጥ ስለ እኛ ነው። እኛ መንፈሳዊውን ነገር የዘራንላችሁ ከሆነ የእናንተን ሥጋዊ በረከት ብናጭድ ትልቅ ነገር መሆኑ ነውን? ሌሎች ይህን ነገር ከእናንተ የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ ታዲያ፥ እኛ ከዚህ የሚበልጥ መብት እንዴት አይኖረንም? እኛ ግን በዚህ መብት አልተጠቀምንም፤ ይህን ማድረጋችንም የክርስቶስ የምሥራች ቃል ከመስፋፋት እንዳይገታ በማሰብ ሁሉን ነገር ታግሠን እንቻል ብለን ነው።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች