የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8:7-13

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8:7-13 አማ05

ነገር ግን ይህን የሚያውቁ፥ ሁሉም አይደሉም፤ አንዳንዶች እስከ አሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ ሥጋን የሚበሉት ለጣዖት እንደ ተሠዋ አድርገው ነው፤ ስለዚህ ኅሊናቸው ደካማ በመሆኑ ይረክሳሉ። ዳሩ ግን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን መብል አይደለም፤ ባንበላም የሚጐድልብን ነገር የለም፤ ብንበላም የምናተርፈው ነገር የለም። ይሁን እንጂ ይህ ነጻነታችሁ በእምነት ላልጠነከሩ ሰዎች መሰናከያ እንዳይሆንባቸው ተጠንቀቁ። “ዕውቀት አለኝ” ብለህ ለጣዖት የተሠዋውን በቤተ ጣዖት ስትበላ በእምነቱ ያልጠነከረ ሰው ቢያይህ ይህ ድርጊትህ ሰውየው ለጣዖት የተሠዋውን እንዲበላ ያደፋፍረው የለምን? ስለዚህ በአንተ “ዐዋቂ ነኝ” ባይነት ክርስቶስ የሞተለትና በእምነቱ ያልጠነከረ ክርስቲያን ይጠፋል ማለት ነው። በዚሁ ሁኔታ ክርስቲያን ወንድሞቻችሁን በመበደልና ደካማ ኅሊናቸውንም በማቊሰል ክርስቶስን ትበድላላችሁ። ስለዚህ ምግብ ክርስቲያን ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ ወንድሜን ላለማሰናከል ስል ከቶ ሥጋ አልበላም።