ስለዚህ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገር ሰው የመተርጐም ችሎታ እንዲኖረው ይጸልይ። በተለያዩ ቋንቋዎች ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል እንጂ አእምሮዬ ፍሬአልባ ነው። ታዲያ፥ ምን ማድረግ ይገባኛል? በመንፈሴ እጸልያለሁ፤ በአእምሮዬም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈሴ እዘምራለሁ፤ በአእምሮዬም ደግሞ እዘምራለሁ። እንዲህማ ካልሆነ አንተ በመንፈስ እግዚአብሔርን ስታመሰግን፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ለምስጋና ጸሎትህ “አሜን” ሊል እንዴት ይችላል? እርግጥ አንተ ያቀረብከው የምስጋና ጸሎት በጥሩ ሁኔታ ነው፤ ነገር ግን ሌላው ሰው አይታነጽበትም። እኔ ከሁላችሁ ይበልጥ በተለያዩ ቋንቋዎች ስለምናገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ነገር ግን በተለያዩ ቋንቋዎች በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ቃሎችን ከምናገር ይልቅ ሌሎችን ለማስተማር ስል በቤተ ክርስቲያን አምስት ቃላትን በሚታወቅ ቋንቋ በአእምሮዬ መናገር እወዳለሁ። ወንድሞቼ ሆይ! ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአስተሳሰባችሁስ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ይልቁንም በአስተሳሰባችሁ የበሰላችሁ ሁኑ። ይህም፦ “ ‘በተለያዩ ቋንቋዎች በሚናገሩ ሰዎችና በባዕድ ሰዎች አፍ ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም’ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ በሕግ ተጽፎአል። ስለዚህ በተለያዩ ቋንቋዎች መናገር ምልክት የሚሆነው ለማያምኑ ሰዎች ነው እንጂ ለሚያምኑ ሰዎች አይደለም፤ የትንቢት ቃል መናገር ግን ምልክት የሚሆነው ለሚያምኑት ሰዎች እንጂ ለማያምኑ ሰዎች አይደለም። ክርስቲያኖች በሚሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ ክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋዎች ቢናገርና የማያውቁ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢመጡ ተናጋሪዎችን “እነዚህ ሰዎች አብደዋል” አይሉምን? ነገር ግን እያንዳንዱ የትንቢት ቃል ቢናገርና የማያምን ወይም የማያውቅ ሰው ቢመጣ በሚሰማው ቃል ሁሉ ይወቀሳል፤ እንዲሁም በሚሰማው ቃል ሁሉ ይፈረድበታል። በልቡ የተሰወረው ነገር ይገለጣል፤ በግንባሩም ተደፍቶ “በእርግጥ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነው!” በማለት ለእግዚአብሔር ይሰግዳል።
1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14:13-25
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos