የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘካርያስ 10

10
እግዚአብሔር ለይሁዳ ይጠነቀቃል
1የበልግ ዝናብ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤
ማዕበሉን ደመና የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፤
እርሱ ለሰዎች በቂ ዝናብን፣
ለእያንዳንዱም የምድርን ተክል ይሰጣል።
2ተራፊም አሳሳች ነገር ይናገራል፤
ሟርተኞች የሐሰት ራእይ ያያሉ፤
የውሸት ሕልም ይናገራሉ፤
ከንቱ መጽናናት ይሰጣሉ፤
ስለዚህ ሕዝቡ እንደ በጎች ተቅበዘበዙ፤
እረኛ በማጣትም ተጨነቁ።
3“ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነድዷል፤
መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ የሰራዊት ጌታ
እግዚአብሔር
መንጋውን የይሁዳ ቤት ይጐበኛልና፤
በጦርነትም ጊዜ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።
4ከይሁዳ፣ የማእዘን ድንጋይ፣
የድንኳን ካስማ፣
የጦርነት ቀስት፣
ገዥም ሁሉ ይወጣል።
5ጠላትን መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ይረጋግጣሉ፤
በአንድነት#10፥5 ወይም ሁሉም ገዦች በአንድነት ማለት ነው 5 እነርሱም እንደ ጦር ሰልፈኛ ይሆናሉ፤
እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋራ ስለ ሆነ ተዋግተው፤
ፈረሰኞችን ያዋርዳሉ።
6“የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤
የዮሴፍንም ቤት እታደጋለሁ።
ስለምራራላቸው፣
ወደ ቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤
እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ሰዎች
ይሆናሉ፤
እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፣
ጸሎታቸውን እሰማለሁ።
7ኤፍሬማውያን እንደ ኀያላን ሰዎች ይሆናሉ፤
ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ሐሤት ያደርጋል።
ልጆቻቸው ያዩታል፤ ደስተኛም ይሆናሉ፤
ልባቸውም በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።
8በፉጨት እጠራቸዋለሁ፤
በአንድነት እሰበስባቸዋለሁ፤
በርግጥ እቤዣቸዋለሁ፤
እንደ ቀድሞው ይበዛሉ።
9በሕዝቦች መካከል ብበትናቸውም፣
በሩቅ ምድር ሆነው ያስቡኛል፤
እነርሱና ልጆቻቸው ተርፈው፣
በሕይወት ይመለሳሉ።
10ከግብጽ እመልሳቸዋለሁ፤
ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፤
ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ አመጣቸዋለሁ፤
በቂ ስፍራም አይገኝላቸውም።
11በመከራ ባሕር ውስጥ ያልፋሉ፤
የባሕሩ ማዕበል ጸጥ ይላል፤
የአባይም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል።
የአሦር ትምክሕት ይዋረዳል፤
የግብጽም በትረ መንግሥት ያበቃል።
12እግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፤
በስሙም ይመላለሳሉ”
ይላል እግዚአብሔር

Currently Selected:

ዘካርያስ 10: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ