መዝሙር 98:1-3
መዝሙር 98:1-3 NASV
ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤ እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጓልና፤ ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም ማዳንን አድርገውለታል። እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ። ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ ታማኝነቱንም ዐሰበ፤ የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን አዩ።