የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 74:16-20

መዝሙር 74:16-20 NASV

ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው፤ ጨረቃንና ፀሓይን አንተ አጸናሃቸው። የምድርን ዳርቻ ሁሉ የወሰንህ አንተ ነህ፤ በጋውንም ክረምቱንም አንተ ሠራህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላት እንዴት እንደሚያሾፍ፣ ሞኝ ሕዝብም ስምህን እንዴት እንዳቃለለ ዐስብ። የርግብህን ነፍስ አሳልፈህ ለዱር አራዊት አትስጥ፤ የችግረኞች ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለሙ አትርሳ። ኪዳንህን ዐስብ፤ የዐመፅ መናኸሪያ በምድሪቱ ጨለማ ስፍራዎች ሞልተዋልና።