የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 7:1-9

መዝሙር 7:1-9 NASV

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝ፤ ታደገኝም፤ አለዚያ እንደ አንበሳ ይዘነጣጥሉኛል፤ የሚያድነኝ በሌለበትም ይቦጫጭቁኛል። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ይህን አድርጌ ከሆነ፣ በደልም በእጄ ከተገኘ፣ በጎ ለዋለልኝ ክፉ መልሼ ብሆን፣ ጠላቴንም በከንቱ ዘርፌ ከሆነ፣ ጠላቴ አሳድዶ ይያዘኝ፤ ሕይወቴን ከምድር ይቀላቅል፤ ክብሬንም ከዐፈር ይደባልቅ። ሴላ እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤ በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ! የሕዝቦች ጉባኤ ይክበብህ፤ አንተም ከላይ ሆነህ ግዛቸው፤ እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል። እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ፤ ልዑል ሆይ፤ እንደ ቅን አካሄዴ መልስልኝ። ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ ጻድቅ አምላክ ሆይ፤ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ ጻድቁን ግን አጽና።