እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ። ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤ እስከ መቼ፣ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል? እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤ በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤ በሲኦልስ ማን ያመሰግንሃል? ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤ መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ። ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤ ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኗቸዋል። እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቷልና። እግዚአብሔር ልመናዬን አድምጧል፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል። ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ እጅግም ይደነግጣሉ፤ በመጡበት ይመለሳሉ፤ ድንገትም ይዋረዳሉ።
መዝሙር 6 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 6
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 6:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos