መዝሙር 47
47
መዝሙር 47
እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ንጉሥና የዓለም ጌታ
ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1ሕዝቦች ሁላችሁ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፤
ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር እልል በሉ።
2በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ የሆነው ንጉሥ፣
ልዑል እግዚአብሔር የሚያስፈራ ነውና።
3ሕዝቦችን ከእኛ በታች አደረገ፤
መንግሥታትንም ከእግራችን ሥር አስገዛልን።
4ለሚወድደው ለያዕቆብ ክብር የሆነችውን፣
ርስታችንን እርሱ መረጠልን። ሴላ
5አምላክ በእልልታ፣
እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።
6አምላካችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤
ንጉሣችንን አወድሱት፤ አወድሱት፤
7እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤
ምርጥ ዝማሬ#47፥7 ዕብራይስጡ ማስኪል ይላል፤ ይኸውም የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የሙዚቃውን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። አቅርቡለት።
8እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ነግሧል፤
እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል።
9ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር፣
የሕዝቦች መኳንንት ተሰበሰቡ፤
የምድር ነገሥታት#47፥9 ወይም ጋሾች የእግዚአብሔር ናቸውና፤
እርሱም እጅግ ከፍ ከፍ ያለ ነው።
Currently Selected:
መዝሙር 47: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.