መዝሙር 18:28-36

መዝሙር 18:28-36 NASV

እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴን ታበራለህ፤ አምላኬ፤ ጨለማዬን ያበራል። በአንተ ጕልበት በሰራዊት ላይ እረማመዳለሁ፤ በአምላኬም ኀይል ቅጥር እዘላለሁ። የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው። መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ፣ ጋሻ ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ? ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው? ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቀና እርሱ እግዚአብሔር ነው። እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ ክንዶቼም የናስ ቀስት መገተር ይችላሉ። የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፤ ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል። ከሥሬ ያለውን ስፍራ ለአረማመዴ አሰፋህልኝ፤ እግሬም አልተንሸራተተም።