ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ። በምኖርበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሕይወትም እስካለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ። በገዦች አትታመኑ፤ ማዳን በማይችሉ ሥጋ ለባሾችም አትመኩ። መንፈሳቸው ትወጣለች፤ ወደ መሬታቸውም ይመለሳሉ፤ ያን ጊዜም ዕቅዳቸው እንዳልነበር ይሆናል። ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው ምስጉን ነው፤ እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በእነዚህም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ፣ ታማኝነቱንም ለዘላለም የሚጠብቅ ነው፤ ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤
መዝሙር 146 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 146
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 146:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos