ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ልመና አቀርባለሁ። ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ፤ ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ። መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣ መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤ በመተላለፊያ መንገዴ ላይ፣ ወጥመድ በስውር ዘርግተውብኛል። ወደ ቀኜ ተመልከት፤ እይም፤ ስለ እኔ የሚገድደው የለም፤ ማምለጫም የለኝም፤ ስለ ነፍሴም ደንታ ያለው የለም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።
መዝሙር 142 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 142
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 142:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos