መዝሙር 137
137
መዝሙር 137
1በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣
ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን።
2እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣
በገናዎቻችንን ሰቀልን።
3የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤
የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤
ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።
4 የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣
እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!
5ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣
ቀኝ እጄ ትክዳኝ።
6ሳላስታውስሽ ብቀር፣
ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣
ምላሴ ከትናጋዬ ጋራ ትጣበቅ።
7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣
ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤
ደግሞም፣ “አፍርሷት፤
ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ።
8አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤
በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሽው ድርጊት፣
የእጅሽን የሚሰጥሽ ብፁዕ ነው፤
9ብፁዕ ነው፤
ሕፃናትሽንም ይዞ፣
በዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ።
Currently Selected:
መዝሙር 137: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.