የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ምሳሌ 4:20-23

ምሳሌ 4:20-23 NASV

ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ። ከእይታህ አታርቀው፤ በልብህም ጠብቀው፤ ለሚያገኘው ሕይወት፤ ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና። ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።