የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 34:13-29

ዘኍል 34:13-29 NASV

ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “ይህችን ምድር ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ደልድሉ፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ለዘጠኙና ለግማሹ ነገድ እንድትሰጥ አዝዟል፤ የሮቤል ነገድ ቤተ ሰቦች፣ የጋድ ነገድ ቤተ ሰቦች እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ተቀብለዋልና። እነዚህ ሁለቱ ነገዶችና እኩሌታው ነገድ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ፣ ከኢያሪኮ ማዶ በፀሓይ መውጫ በኩል ርስታቸውን ተቀብለዋል።” እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚያከፋፍሏችሁ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፤ ምድሪቱን በማከፋፈሉ እንዲረዱም ከየነገዱ አንዳንድ መሪ ውሰዱ። “ስማቸውም ይህ ነው፤ “ከይሁዳ ነገድ፣ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፤ ከስምዖን ነገድ፣ የዓሚሁድ ልጅ ሰላሚኤል፤ ከብንያም ነገድ፣ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፤ የዳን ነገድ መሪ፣ የዩግሊ ልጅ ቡቂ፤ የዮሴፍ ልጅ የምናሴ ነገድ መሪ፣ የሱፊድ ልጅ አኒኤል፤ የዮሴፍ ልጅ የኤፍሬም ነገድ መሪ፣ የሺፍጣን ልጅ ቀሙኤል፤ የዛብሎን ነገድ መሪ፣ የፈርናክ ልጅ ኤሊሳፈን፤ የይሳኮር ነገድ መሪ፣ የሖዛ ልጅ ፈልጢኤል፤ የአሴር ነገድ መሪ፣ የሴሌሚ ልጅ አሒሁድ፤ የንፍታሌም ነገድ መሪ፣ የዓሚሁድ ልጅ ፈዳሄል።” እነዚህ በከነዓን ምድር ለእስራኤላውያን ርስት እንዲያከፋፍሉ እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዛቸው ሰዎች ናቸው።