ዘኍልቍ 33
33
እስራኤላውያን ከግብጽ እስከ ሞዓብ ሲጓዙ የሰፈሩባቸው ቦታዎች
1እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ወጥተው፣ በጕዞ ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፤ 2ሙሴም በጕዟቸው ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸውን ቦታዎች በእግዚአብሔር ትእዛዝ መዘገበ፤ በየቦታው እየሰፈሩ ያደረጉት ጕዞም ይህ ነው፦
3እስራኤላውያን በመጀመሪያው ወር በዐሥራ ዐምስተኛውም ቀን በፋሲካ ማግስት ከራምሴ ተነሡ፤ ግብጻውያን ሁሉ እያዩአቸውም በልበ ሙሉነት ተጓዙ። 4በዚህ ጊዜ ግብጻውያን እግዚአብሔር ከመካከላቸው የገደለባቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ እግዚአብሔር በግብጽ አማልክት ላይ ፈርዶ ነበርና።
5እስራኤላውያን ከራምሴ ተነሥተው በሱኮት ሰፈሩ።
6ከሱኮትም ተነሥተው በምድረ በዳው ዳርቻ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ።
7ከኤታም ተነሥተው ከበኣልዛፎን በስተምሥራቅ ወዳለችው ወደ ፊሀሒሮት በመመለስ በሚግዶል አጠገብ ሰፈሩ።
8ከፊሃሒሮት#33፥8 ብዙ የማሶሬቲክ፣ የኦሪተ ሳምራውያንና የቩልጌት ቅጆች ከፊሃሒሮት ተነሥተው የሚሉ ሲሆን፤ አያሌ የማሶሬቲክ ቅጆች ግን ከፊሃሒሮት ፊት ለፊት ተነሥተው ይላሉ። ተነሥተው በባሕሩ ውስጥ በማለፍ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ ከዚያም በኤታም ምድረ በዳ ሦስት ቀን ተጕዘው በማራ ሰፈሩ።
9ከማራ ተነሥተው ዐሥራ ሁለት የውሃ ምንጮችና ሰባ የተምር ዛፎች ወደ ነበሩበት ወደ ኤሊም መጥተው በዚያ ሰፈሩ።
10ከኤሊም ተነሥተው በቀይ ባሕር#33፥10 በዕብራይስጥ ያም ሱፍ የሚል ሲሆን፣ የደንገል ባሕር ማለት ነው። አጠገብ ሰፈሩ።
11ከቀይ ባሕር ተነሥተው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።
12ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው በራፍቃ ሰፈሩ።
13ከራፍቃ ተነሥተው በኤሉስ ሰፈሩ።
14ከኤሉስ ተነሥተው በራፊዲም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጣው ውሃ አልነበረም።
15ከራፊዲም ተነሥተው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።
16ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው በቂብሮት ሃታአባ ሰፈሩ።
17ከቂብሮት ሃታአባ ተነሥተው በሐጼሮት ሰፈሩ።
18ከሐጼሮት ተነሥተው በሪትማ ሰፈሩ።
19ከሪትማ ተነሥተው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ።
20ከሬሞን ዘፋሬስ ተነሥተው በልብና ሰፈሩ።
21ከልብና ተነሥተው በሪሳ ሰፈሩ።
22ከሪሳ ተነሥተው በቀሄላታ ሰፈሩ።
23ከቀሄላታ ተነሥተው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ።
24ከሻፍር ተራራ ተነሥተው በሐራዳ ሰፈሩ።
25ከሐራዳ ተነሥተው በማቅሄሎት ሰፈሩ።
26ከማቅሄሎት ተነሥተው በታሐት ሰፈሩ።
27ከታሐት ተነሥተው በታራ ሰፈሩ።
28ከታራ ተነሥተው በሚትቃ ሰፈሩ።
29ከሚትቃ ተነሥተው በሐሽሞና ሰፈሩ።
30ከሐሽሞና ተነሥተው በምሴሮት ሰፈሩ።
31ከምሴሮት ተነሥተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ።
32ከብኔያዕቃን ተነሥተው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ።
33ከሖርሃጊድጋድም ተነሥተው በዮጥባታ ሰፈሩ።
34ከዮጥባታ ተነሥተው በዔብሮና ሰፈሩ።
35ከዔብሮና ተነሥተው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ።
36ከዔጽዮንጋብር ተነሥተው በጺን ምድረ በዳ ባለችው በቃዴስ ሰፈሩ።
37ከቃዴስ ተነሥተው በኤዶም ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ። 38በእግዚአብሔር ትእዛዝ ካህኑ አሮን ወደ ሖር ተራራ ወጣ፤ እዚያም እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በአርባኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። 39አሮን በሖር ተራራ ላይ ሲሞት፣ ዕድሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበር።
40በከነዓን በምትገኘው በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ፣ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ።
41እነርሱም ከሖር ተራራ ተነሥተው በሴልሞና ሰፈሩ።
42ከሴልሞና ተነሥተው በፋኖን ሰፈሩ።
43ከፋኖን ተነሥተው በአቦት ሰፈሩ።
44ከአቦት ተነሥተው በሞዓብ ዳርቻ በምትገኘው በዒዮዓባሪም ሰፈሩ።
45ከጋይም ተነሥተው በዲቦንጋድ ሰፈሩ።
46ከዲቦንጋድ ተነሥተው በዓልሞን ዲብላታይም ሰፈሩ።
47ከዓልሞን ዲብላታይም ተነሥተው በናባው አጠገብ በሚገኙት በዓባሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ።
48ከዓባሪም ተራሮች ተነሥተው ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ። 49እዚያም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልስጢም ባለው ስፍራ ሰፈሩ።
50ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ፣ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 51“እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ወደ ከነዓን ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገሩ፣ 52የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አሳድዳችሁ አስወጧቸው፤ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን በሙሉ አጥፉ፤ እንዲሁም በኰረብታ ላይ የተሠሩትን መስገጃዎቻቸውን ሁሉ አፈራርሱ። 53ምድሪቱን ርስት አድርጌ ሰጥቻችኋለሁና ውረሷት፤ ኑሩባትም። 54ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን።
55“ ‘የምድሪቱን ነዋሪዎች አሳድዳችሁ ሳታስወጧቸው ብትቀሩ ግን፣ እንዲኖሩ የተዋችኋቸው ሰዎች ለዐይናችሁ ስንጥር፣ ለጐናችሁም እሾኽ ይሆኑባችኋል፤ በምትኖሩበትም ምድር ችግር ይፈጥሩባችኋል። 56እኔም በእነርሱ ላይ ለማድረግ ያሰብሁትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።’ ”
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.