የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 27:18-23

ዘኍል 27:18-23 NASV

ስለዚህም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “መንፈስ ቅዱስ ያደረበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት። በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበር ፊት እንዲቆም አድርገው፤ በፊታቸውም ሹመው፤ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲታዘዝለትም ከሥልጣንህ ከፍለህ ስጠው። እርሱም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ሆኖ በኡሪም በመጠየቅ ውሳኔ በሚያስገኝለት በካህኑ በአልዓዛር ፊት ይቆማል፤ እርሱም ሆነ መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በአልዓዛር ትእዛዝ ይወጣሉ፤ በእርሱም ቃል ይገባሉ።” ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው አደረገ፤ ኢያሱንም ወስዶ በካህኑ በአልዓዛርና በመላው የእስራኤል ማኅበር ፊት አቆመው፤ ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ አማካይነት ባዘዘው መሠረት እጁን በራሱ ላይ ጭኖ ሾመው።