የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሚክያስ 5:1-6

ሚክያስ 5:1-6 NASV

አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤ ከበባ ተደርጎብናልና። የእስራኤልን ገዥ፣ ጕንጩን በበትር ይመቱታል። “አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልኛል።” ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣ እስራኤል ትተዋለች፤ የተቀሩት ወንድሞቹም፣ ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ። በእግዚአብሔር ኀይል፣ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣ ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል። በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣ ተደላድለው ይኖራሉ። እርሱም ሰላማቸው ይሆናል። አሦራዊ ምድራችንን ሲወርር፣ ምሽጎቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ ሰባት እረኞችን፣ እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን። የአሦርን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩድን ምድር በተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ፤ አሦራዊው ምድራችንን ሲወርር፣ ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣ እርሱ ነጻ ያወጣናል።