YouVersion Logo
Search Icon

ማቴዎስ 4:18, 19, 20, 21, 22, 23, 24, 25

ማቴዎስ 4:18 NASV

ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፣ ሁለት ወንድማማቾች ማለትም፣ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንንና ወንድሙን እንድርያስን አያቸው። ዓሣ አጥማጆች ነበሩና መረባቸውን ወደ ባሕሩ ይጥሉ ነበር።

ማቴዎስ 4:19 NASV

ኢየሱስም፣ “ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው።

ማቴዎስ 4:20 NASV

ወዲያው መረባቸውን ትተው ተከተሉት።

ማቴዎስ 4:21 NASV

ዐለፍ እንዳለም፣ ሌሎች ሁለት ወንድማማቾች፣ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን አየ። ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ውስጥ መረባቸውን ያበጁ ነበር። ኢየሱስም ጠራቸው፤

ማቴዎስ 4:22 NASV

ወዲያውኑ ጀልባቸውንም ሆነ አባታቸውን ትተው ተከተሉት።

ማቴዎስ 4:23 NASV

ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፣ በሕዝቡ መካከል ማንኛውንም ደዌና ሕመም እየፈወሰ በመላው ገሊላ ይዘዋወር ነበር።

ማቴዎስ 4:24 NASV

ከዚህም የተነሣ ዝናው በመላዋ ሶርያ ተሰማ፤ ሕዝቡም በተለያዩ በሽታዎች የታመሙትን፣ በክፉ ደዌ የሚሠቃዩትን፣ አጋንንት ያደሩባቸውን፣ የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።

ማቴዎስ 4:25 NASV

ከዚህም የተነሣ ከገሊላ፣ ከ “ዐሥሩ ከተሞች”፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ማዶ የመጡ ብዙ ሰዎች ተከተሉት።