YouVersion Logo
Search Icon

ማቴዎስ 17:22, 23, 24, 25, 26, 27

ማቴዎስ 17:22 NASV

በገሊላ ተሰባስበው ሳሉ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ዐልፎ ይሰጣል፤

ማቴዎስ 17:23 NASV

እነርሱም ይገድሉታል፤ እርሱም በሦስተኛው ቀን ይነሣል።” ደቀ መዛሙርቱም እጅግ ዐዘኑ።

ማቴዎስ 17:24 NASV

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ቅፍርናሆም ከደረሱ በኋላ፣ የቤተ መቅደሱ ግብር ተቀባዮች ወደ ጴጥሮስ ቀርበው “መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር የቤተ መቅደስ ግብር አይከፍልምን?” አሉት።

ማቴዎስ 17:25 NASV

እርሱም፣ “ይከፍላል እንጂ” አላቸው። ጴጥሮስ ወደ ቤት እንደ ገባ ኢየሱስ በቅድሚያ፣ “ስምዖን፤ የምድር ነገሥታት ግብር ወይም ቀረጥ የሚቀበሉት ከራሳቸው ልጆች ወይስ ከሌሎች ይመስልሃል?” አለው።

ማቴዎስ 17:26 NASV

ጴጥሮስም፣ “ከሌሎች ነው የሚቀበሉት” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለ፤ “እንግዲያውስ ልጆች ነጻ ናቸው፤

ማቴዎስ 17:27 NASV

ሆኖም እንዳናስቀይማቸው ሄደህ መንጠቈህን ወደ ባሕር ጣል፤ መጀመሪያ የምትይዘውን ዓሣ አፉን ስትከፍት የምታገኘውን አንድ እስታቴር በእኔና በአንተ ስም ክፈል።”