የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ማቴዎስ 16:21-23

ማቴዎስ 16:21-23 NASV

ኢየሱስ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ፣ በዚያም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በኦሪት ሕግ መምህራን እጅ መከራን ይቀበልና ይገደል ዘንድ፣ በሦስተኛው ቀን ከሞት ይነሣ ዘንድ እንደሚገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጽላቸው ጀመር። ጴጥሮስም ኢየሱስን ወደ ጐን ሳብ አድርጎ፣ “ጌታ ሆይ፤ እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይድረስብህ” እያለ ይገሥጸው ጀመር። ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ዘወር ብሎ፣ “አንተ ሰይጣን፣ ወደ ኋላዬ ሂድ፤ የሰው እንጂ የእግዚአብሔር ነገር በዐሳብህ ስለሌለ መሰናክል ሆነህብኛል!” አለው።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች