ከዕለታቱ በአንድ ቀን፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጀልባ ላይ ወጣ፤ ኢየሱስም፤ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው፤ ከዚያም ጕዞ ቀጠሉ። እየተጓዙ ሳሉም ኢየሱስ እንቅልፍ ወስዶት ተኛ፤ በዚህ ጊዜ በባሕሩ ላይ ማዕበል ተነሣ፤ ውሃውም ጀልባዋን ዘልቆ ስለ ገባ፣ አደጋ አፋፍ ላይ ደረሱ። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፣ “ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ ማለቃችን እኮ ነው!” እያሉ ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የውሃውን መናወጥ ገሠጸ፤ በዚህ ጊዜ ነፋሱም ነውጡም ተወ፤ ጸጥታም ሆነ። እርሱም ደቀ መዛሙርቱን፣ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነርሱም በፍርሀትና በመደነቅ፣ “ይህ ነፋስንና ውሃን የሚያዝ፣ እነርሱም የሚታዘዙለት እርሱ ማን ነው?” ተባባሉ።
ሉቃስ 8 ያንብቡ
ያዳምጡ ሉቃስ 8
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሉቃስ 8:22-25
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos