YouVersion Logo
Search Icon

ሉቃስ 15:1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10

ሉቃስ 15:1 NASV

አንድ ቀን፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኀጢአተኞች ሁሉ ሊሰሙት በዙሪያው ተሰበሰቡ።

ሉቃስ 15:2 NASV

ፈሪሳውያንና ጸሐፍትም፣ “ይህ ሰው ኀጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋራ ይበላል” እያሉ አጕረመረሙ።

ሉቃስ 15:3 NASV

ኢየሱስም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤

ሉቃስ 15:4 NASV

“ከእናንተ መካከል አንዱ መቶ በጎች ቢኖሩትና ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት፣ ዘጠና ዘጠኙን በሜዳ ላይ ጥሎ የጠፋውን እስኪያገኝ ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ማን ነው?

ሉቃስ 15:5 NASV

ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ተሸክሞ፣

ሉቃስ 15:6 NASV

ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹንም በአንድነት ጠርቶ፣ ‘የጠፋውን በጌን አግኝቻለሁና ከእኔ ጋራ ደስ ይበላችሁ’ ይላቸዋል።

ሉቃስ 15:7 NASV

እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ፣ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።

ሉቃስ 15:8 NASV

“ወይም ዐሥር የብር ሳንቲሞች ያላት ሴት ከዐሥሩ አንዱ ቢጠፋባት፣ እስክታገኘው ድረስ መብራት አብርታ፣ ቤቷን ጠርጋ፣ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?

ሉቃስ 15:9 NASV

ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆቿንና ጎረቤቶቿን በአንድነት ጠርታ፣ ‘የጠፋብኝን የብር ሳንቲም አግኝቻለሁና ከእኔ ጋራ ደስ ይበላችሁ’ ትላቸዋለች።

ሉቃስ 15:10 NASV

እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።”