ኢዮብ 26
26
ኢዮብ
1ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
2“ኀይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!
ደካማውንስ ምንኛ አዳንኸው!
3ጥበብ የሌለውን ምንኛ መከርኸው!
ታላቅ ዕውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!
4ይህን ቃል እንድትናገር የረዳህ ማን ነው?
የማንስ መንፈስ በአንደበትህ ተጠቀመ?
5“ከውሆችና በውስጣቸው ከሚኖሩ በታች ያሉ፣
የሙታን መንፈስ በጭንቅ ላይ ናቸው።
6ሲኦል#26፥6 የዕብራይስጡ ቅጅ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ አንዳንድ ቅጆች ግን፣ ሞት ይላሉ። በአምላክ ፊት ዕራቍቷን ናት፤
የጥፋትንም#26፥6 ዕብራይስጡ፣ አባዶን ይላል። ስፍራ የሚጋርድ የለም።
7የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋው፤
ምድርንም እንዲያው በባዶው ላይ አንጠለጠላት።
8ውሆችን በደመናዎቹ ይጠቀልላል፤
ክብደታቸውም ደመናዎቹን አይሸነቍርም።
9ደመናዎቹን በላዩ ዘርግቶ፣
የሙሉውን ጨረቃ ፊት ይጋርዳል።
10ለብርሃንና ለጨለማ ድንበር ይሆን ዘንድ፣
በውሆች ላይ የአድማስ ክበብ አበጀ።
11የሰማይ ምሰሶዎች ይንቀጠቀጣሉ፤
በተግሣጹም ይደነግጣሉ።
12በኀይሉ ባሕርን ያናውጣል፤
በጥበቡም ረዓብን ይቈራርጣል።
13በእስትንፋሱ ሰማያትን አጠራ፤
እጁም ተወርዋሪውን እባብ ወጋች።
14እነዚህ የሥራው ዳር ዳር ናቸው፤
ስለ እርሱ የሰማነው ምንኛ አነስተኛ ነው!
የኀይሉንስ ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?”
Currently Selected:
ኢዮብ 26: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.