መሳፍንት 3:28-31

መሳፍንት 3:28-31 NASV

እርሱም፣ “ጠላታችሁን ሞዓብን እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ስለ ሰጣችሁ ተከተሉኝ” በማለት አዘዛቸው፤ እነርሱም ተከትለውት ወረዱ፤ ከዚያም ከዮርዳኖስ ወደ ሞዓብ የሚያሻግሩትን መልካዎች በመያዝ አንድም ሰው እንዳያልፍ ከለከሉ። በዚያ ጊዜ ብርቱና ኀይለኛ የሆኑ ዐሥር ሺሕ ሞዓባውያንን ገደሉ፤ አንድም ሰው አላመለጠም። በዚያ ቀን ሞዓብ በእስራኤል ድል ሆነች፤ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ሰላም አገኘች። ከናዖድ በኋላ ስድስት መቶ ፍልስጥኤማውያንን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሰሜጋር ተነሣ፤ እርሱም እንደዚሁ ደግሞ እስራኤልን አዳነ።