ኢሳይያስ 35
35
የተቤዠ ሕዝብ ደስታ
1ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤
በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤
እንደ አደይም ያብባል።
2በደስታና በዝማሬ ሐሤት ያደርጋል፤
የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤
የቀርሜሎስንና የሳሮንን ግርማ ይለብሳል።
የአምላካችንን ታላቅ ግርማ፣
የእግዚአብሔርን ክብር ያያሉ።
3የደከሙትን እጆች አበርቱ፤
የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ፤
4የሚፈራ ልብ ላላቸው እንዲህ በሉ፤
“በርቱ፤ አትፍሩ፤
አምላካችሁ ይመጣል፤
ሊበቀል ይመጣል፤
እርሱም ብድራቱን ይዞ፣
ሊያድናችሁ ይመጣል።”
5በዚያ ጊዜም የዕውር ዐይኖች ይገለጣሉ፤
የደንቈሮም ጆሮዎች ይከፈታሉ።
6ዐንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፤
የድዳውም አንደበት በደስታ ይዘምራል፤
ውሃ ከበረሓ ይወጣል፤
ምንጮችም ከምድረ በዳ ይፈልቃሉ።
7ንዳዳማው ምድር ኵሬ ይሆናል፤
የተጠማው መሬት ውሃ ያመነጫል።
ቀበሮዎች በተኙባቸው ጕድጓዶች፣
ሣር፣ ሸንበቆና ደንገል ይበቅልበታል።
8በዚያ አውራ ጐዳና ይሆናል፤
የተቀደሰ መንገድ ተብሎ ይጠራል።
የረከሱ አይሄዱበትም፤
በመንገዱ ላይ ላሉት ብቻ ይሆናል፤
ቂሎችም አይሄዱም።
9አንበሳ አይኖርበትም፤
ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፤
እነዚህማ በዚያ ስፍራ አይገኙም፤
የዳኑት ብቻ በዚያ ይሄዳሉ፤
10 እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤
በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤
ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤
ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤
ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
Currently Selected:
ኢሳይያስ 35: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.