የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 31

31
በግብጽ ለሚደገፉ ወዮላቸው
1ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣
ከእግዚአብሔርም ርዳታን ለማይሹ፣
ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብጽ ለሚወርዱ፣
በፈረሶች ለሚታመኑ፣
በሠረገሎቻቸው ብዛት፣
በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው!
2እርሱም ግን ጠቢብ ነው፤ ጥፋትን ያመጣል፤
ቃሉን አያጥፍም።
በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣
በደለኞችንም በሚረዱ ላይ ይነሣል።
3ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤
ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤
እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣
ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤
ተረጂውም ይወድቃል፤
ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
4 እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤
“አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል
የሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣
ብዙ እረኞች
ተጠራርተው ሲመጡበት፣
ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣
በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።
5በዐናት ላይ እንደሚያንዣብቡ ወፎች፣
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲሁ ይጋርዳታል፤
ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤
በላይዋ ያልፋል፤ ያድናታልም።”
6እናንተ እስራኤላውያን ሆይ፤ እጅግ ወዳመፃችሁበት ወደ እርሱ ተመለሱ። 7በዚያ ቀን በኀጢአት የተሞላ እጃችሁ የሠራቸውን የወርቅና የብር ጣዖቶች ሁላችሁም ትጥላላችሁና።
8“አሦር የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤
የሥጋ ለባሽ ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል።
ከሰይፍ ፊት ይሸሻል፤
ጕልማሶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ።
9ጠንካራ ምሽጉ በሽብር ምክንያት ይወድቃል፤
መሪዎቹም የጦር ዐርማ ሲያዩ
በድንጋጤ ይዋጣሉ”
ይላል እሳቱ በጽዮን፣
ማንደጃውም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር

Currently Selected:

ኢሳይያስ 31: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ