የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዕንባቆም 1

1
1ነቢዩ ዕንባቆም የተቀበለው ንግር፤
የዕንባቆም ማጕረምረም
2 እግዚአብሔር ሆይ፤
ለርዳታ እየተጣራሁ፣
አንተ የማትሰማው፣
“ግፍ በዛ” ብዬ እየጮኽሁ፣
አንተ የማታድነው እስከ መቼ ነው?
3ስለ ምን በደልን እንዳይ አደረግኸኝ?
እንዴትስ ግፍ ሲፈጸም ትታገሣለህ?
ጥፋትና ግፍ በፊቴ አለ፤
ጠብና ግጭት በዝቷል።
4ስለዚህ ሕግ ደክሟል፤
ፍትሕ ድል አይነሣም፤
ፍትሕ ይጣመም ዘንድ፣
ክፉዎች ጻድቃንን ይከብባሉ።
የእግዚአብሔር መልስ
5“ተመልከቱ፤ ማንም ቢነግራችሁ እንኳ፣
የማታምኑትን ነገር፣
በዘመናችሁ ስለማደርግ፣
ሕዝቡን እዩ፤
እጅግም ተደነቁ።
6የራሳቸው ያልሆኑትን መኖሪያ ስፍራዎች ለመያዝ፣
ምድርን ሁሉ የሚወርሩትን፣
ጨካኝና ፈጣን የሆኑትን፣
ባቢሎናውያንን#1፥6 ከለዳውያን ማለት ነው። አስነሣለሁ።
7እነርሱም የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፤
ፍርዳቸውና ክብራቸው፣
ከራሳቸው ይወጣል።
8ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች፣
ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው።
ፈረሰኞቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤
ከሩቅ ስፍራም ይመጣሉ።
ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ፤
9ሁሉም ለዐመፅ ታጥቀው ይመጣሉ።
ሰራዊታቸው#1፥9 የዕብራይስጡ ቃል ትርጕም በትክክል አይታወቅም። እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ወደ ፊት ይገሠግሣል፤
ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባል።
10ነገሥታትን ይንቃል፤
በገዦችም ላይ ያፌዛል፤
በምሽግ ሁሉ ላይ ይሥቃል፤
የዐፈር ቍልል ሠርቶም ይይዘዋል።
11ከዚያም በኋላ እንደ ነፋስ ዐልፎ ይሄዳል፤
ጕልበታቸውን አምላካቸው ያደረጉ በደለኞች ናቸው።”
የዕንባቆም ዳግመኛ ማጕረምረም
12 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቀድሞው ያለህ አይደለህምን?
የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ አትሞትም#1፥12 ይህ ቃል የተተረጐመው በጥንት የዕብራይስጥ ቅጅ መሠረት ሲሆን የማሶሬቲክ ጽሑፍ አንሞትም ይላል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርድ ሾመኸዋል፤
ዐለት ሆይ፤ ይቀጣ ዘንድ ሥልጣን ሰጥተኸዋል።
13ዐይኖችህ ክፉውን እንዳያዩ እጅግ ንጹሓን ናቸው፤
አንተ በደልን መመልከት አትችልም፤
ታዲያ፣ አታላዮችን ለምን ትመለከታለህ?
ክፉው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠውስ፣
ለምን ዝም ትላለህ?
14ሰዎችን በባሕር ውስጥ እንዳለ ዓሣ፣
ገዥ እንደሌላቸውም እንደሚርመሰመሱ ፍጥረታት አደረግህ።
15ሁሉንም በመንጠቆ ያወጣቸዋል፤
በመረቡ ይይዛቸዋል፤
በወጥመዱ ውስጥ ይሰበስባቸዋል፤
በዚህም ይደሰታል፤ ሐሤትም ያደርጋል።
16ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፤
ለወጥመዱም ያጥናል።
በእነርሱ ተዝናንቶ ይኖራልና፤
ምግቡም ሠብቷል።
17ታዲያ መረቡን ባለማቋረጥ መጣል፣
ሕዝቦችንስ ያለ ርኅራኄ መግደል አለበትን?

Currently Selected:

ዕንባቆም 1: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ