እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) ሙሴን አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ። ሁሉን የሚችል አምላክ (ኤሎሂም) ሆኜ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) በተባለው ስሜ ራሴን አልገለጥሁላቸውም። በእንግድነት የሚኖሩባትን የከነዓንን ምድር እንድሰጣቸው ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ። ደግሞም በግብፃውያን ሥር በባርነት ሆነው ያሰሙትን የእስራኤላውያንን የሥቃይ ድምፅ ሰምቻለሁ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ። “ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ፤ ከግብፃውያን ቀንበር አወጣችኋለሁ። ለእነርሱ ባሪያ ከመሆን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ በተዘረጋች ክንድና በታላቅ ፍርድ እቤዣችኋለሁ። የራሴ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላክ (ኤሎሂም) እሆናችኋለሁ ከግብፃውያን ቀንበር ያላቀቅኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) መሆኔንም ታውቃላችሁ። ከዚያም ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ እሰጣችኋለሁ ብዬ ወደማልሁላቸው ምድር አመጣችኋለሁ፤ ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ። እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ” ሙሴ ይህን ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ ተስፋ ከመቍረጣቸውና ከአስከፊ እስራታቸው የተነሣ ግን አላዳመጡትም። ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሂድና ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን እስራኤላውያን ከአገሩ እንዲወጡ ይፈቅድላቸው ዘንድ ንገረው።” ሙሴ ግን እግዚአብሔርን (ያህዌ)፣ “እስራኤላውያን ያልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል፤ እኔ ለራሴ ተብታባ ሰው ነኝ” አለው። በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር (ያህዌ) ስለ እስራኤላውያንና ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ለሙሴና ለአሮን ነገራቸው፤ እስራኤላውያንንም ከግብፅ እንዲያወጡ አዘዛቸው።
ዘፀአት 6 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘፀአት 6
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘፀአት 6:2-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos