የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘዳግም 19:14-21

ዘዳግም 19:14-21 NASV

አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ለአንተ በሚተላለፍልህ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አታንሣ። በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍ ሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ፣ አንድ ምስክር አይበቃም፤ ጕዳዩ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት መረጋገጥ አለበት። ተንኰለኛ የሆነ ምስክር አንድን ሰው በሐሰት ቢከስስ፣ ክርክሩ የሚመለከታቸው ሁለቱ ሰዎች በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት፣ በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ። ፈራጆችም ጕዳዩን በጥልቅ ይመርምሩት፤ ያም ምስክር በወንድሙ ላይ በሐሰት የመሰከረ መሆኑ ከተረጋገጠ፣ በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያሰበውን በእርሱ ላይ አድርጉበት፤ ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ። የቀሩትም ሰዎች ይህን ሰምተው ይፈራሉ፤ እንዲህ ያለው ክፉ ነገርም ለወደፊቱ በመካከልህ ከቶ አይደገምም። ርኅራኄ አታድርግ፤ ሕይወት በሕይወት፣ ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በእግር ይመለስ።