እንግዲህ ልጄ ሆይ፤ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ። በብዙ ምስክር ፊት ከእኔ የሰማኸውን፣ ሌሎችን ለማስተማር ብቃት ላላቸው ለታመኑ ሰዎች ዐደራ ስጥ። እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ በጎ ወታደር ከእኛ ጋር መከራን ተቀበል። በውትድርና የሚያገለግል ሰው አዛዡን ለማስደሰት ይጥራል እንጂ በሌላ ሥራ ራሱን አያጠላልፍም። እንደዚሁም በውድድር የሚሳተፍ ሰው፣ የውድድሩን ሕግ ጠብቆ ካልተወዳደረ የድሉን አክሊል አያገኝም። ትጉህ ገበሬም ከሰብሉ ለመጠቀም የመጀመሪያው ሊሆን ይገባዋል። እኔ የምለውን ልብ በል፤ ጌታ በሁሉም ነገር ማስተዋልን ይሰጥሃልና። ከሙታን የተነሣውን፣ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ዐስብ፤ የእኔም ወንጌል ይኸው ነው፤ ለዚህም እንደ ወንጀለኛ እስከ መታሰር ድረስ መከራን እየተቀበልሁ ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም። ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እነርሱም ያገኙ ዘንድ፣ ለተመረጡት ስል ሁሉንም በመታገሥ እጸናለሁ። እንዲህ የሚለው ቃል የታመነ ነው፤ ከእርሱ ጋር ከሞትን፣ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን። ብንጸና፣ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን። ብንክደው፣ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤ ታማኞች ሆነን ባንገኝ፣ እርሱ ታማኝ እንደ ሆነ ይኖራል፤ ራሱን መካድ አይችልምና።
2 ጢሞቴዎስ 2 ያንብቡ
ያዳምጡ 2 ጢሞቴዎስ 2
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 2 ጢሞቴዎስ 2:1-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos