የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ዜና መዋዕል 4

4
የቤተ መቅደሱ ዕቃዎች መሟላት
4፥2-64፥10–5፥1 ተጓ ምብ – 1ነገ 7፥23-267፥38-51
1ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱ ዐሥር ክንድ#4፥1 ርዝመቱና ወርዱ 9 ሜትር ቁመቱ 4.5 ሜትር ያህል ነው። የሆነ የናስ መሠዊያ ሠራ። 2እንዲሁም ስፋቱ ከጠርዝ እስከ ጠርዝ ዐሥር ክንድ፣ ቁመቱ ዐምስት#4፥2 2.3 ሜትር ያህል ነው። ክንድ የሆነ ክብ ገንዳ ከቀለጠ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ#4፥2 14 ሜትር ይህል ነው። ሆነ። 3ከገንዳው ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኰርማ ቅርጾች#4፥3 45 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው። ነበሩበት፤ ኰርማዎቹም ከገንዳው ጋራ አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር።
4ገንዳውም፣ ሦስቱ ፊታቸውን ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ባዞሩ የዐሥራ ሁለት በሬዎች ምስሎች ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ገንዳው በላያቸው ሆኖ የሁሉም የኋላ አካል በመካከል ላይ የገጠመ ነበር። 5የገንዳው ውፍረት አንድ ስንዝር#4፥5 7.5 ሳንቲ ሜትር ያህል ነው። ሲሆን፣ የከንፈሩ ጠርዝ ደግሞ የአበባ ቅርጽ ያለው የጽዋ ከንፈር የመሰለ ነው፤ ይህም ሦስት ሺሕ የባዶስ መስፈሪያ#4፥5 6600 ሊትር ያህል ነው። ያህል ውሃ የሚይዝ ነው።
6እንዲሁም ዐሥር የመታጠቢያ ገንዳዎች አሠርቶ ዐምስቱን በደቡብ፣ ዐምስቱን ደግሞ በሰሜን በኩል አስቀመጠ፤ ገንዳዎቹ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡት ነገሮች የሚታጠቡባቸው ሲሆኑ፣ ገንዳው ግን ለካህናት መታጠቢያ የሚያገለግል ነበር።
7በተሰጠው የአሠራር መመሪያ መሠረት፣ ዐሥር የወርቅ መቅረዞች ሠርቶ ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት፣ ዐምስቱን በስተ ደቡብ፣ ዐምስቱን በስተሰሜን አኖራቸው።
8ዐሥር ጠረጴዛ ሠርቶም ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት ዐምስቱን በስተ ደቡብ፣ ዐምስቱን ደግሞ በስተሰሜን በኩል አኖራቸው፤ ደግሞም አንድ መቶ ጐድጓዳ የወርቅ ሳሕኖች ሠራ።
9የካህናቱንም አደባባይ ሠራ፤ እንዲሁም ታላቁን አደባባይና በሮቹን ከሠራ በኋላ በናስ ለበጣቸው። 10ገንዳውንም ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ ምሥራቅ ባለው ማእዘን በቀኝ በኩል አኖረው።
11ኪራምም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን ሠራ።
ኪራምም ለአምላክ ቤተ መቅደስ አገልግሎት ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራውን ሥራ ፈጸመ እነዚህም፦
12ሁለቱን አዕማድ፣
በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ሁለት ባለሳሕን ጕልላቶችን፤
በአዕማዱ ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ሁለት ጕልላቶችን ያስጌጡትን ሁለት መረቦች፤
13በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ጕልላቶች የሚሸፍኑና በሁለት ረድፍ የተቀረጹትን መረቦች የሚያስጌጡትን አራት መቶ ሮማኖች፤
14መቆሚያዎች ከነመታጠቢያ ገንዳዎቻቸው፤
15ገንዳውና ከሥሩ ያሉትን ዐሥራ ሁለት ኰርማዎች፤
16ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ሜንጦዎችንና ከእነዚሁም ጋራ የተያያዙ ዕቃዎች።
ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር። 17ንጉሡም እነዚህ ዕቃዎች በዮርዳኖስ ሸለቆ፣ በሱኮትና በጸሬዳ መካከል ባለው በሸክላ ዐፈር ቦታ ቀልጠው በሸክላ ቅርጽ ተሠርተው እንዲወጡ አደረገ። 18እነዚህ ሰሎሞን ያሠራቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ ብዙዎች ስለ ሆኑ የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበር አልታወቀም።
19እንደዚሁም ሰሎሞን ለቤተ መቅደስ መገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሠራ፤ እነዚህም፦
የወርቅ መሠዊያ፣
የገጸ ኅብስቱ ጠረጴዛ፣
20በተሰጠው መመሪያ መሠረት፣ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት እንዲነድዱ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞች ከነቀንዲሎቻቸው፣
21ከወርቅ የተቀረጹ አበባዎችን እና ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መኰስተሪያዎችን፤
22ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ የመብራት መኰስተሪያዎች፣ ለመርጨት የሚያገለግሉ ጐድጓዳ ሳሕኖች፣ ጭልፋዎችና ጥናዎች፣ እንደዚሁም የቤተ መቅደሱ የወርቅ መዝጊያዎች፣ ይኸውም የቅድስተ ቅዱሳኑ የውስጠኛው መዝጊያዎችና የቤተ መቅደሱ አዳራሽ መዝጊያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ